Header image m
AWI ZONE HIGH COURT
Tel+251-058-227-0041 Fax +251-058-227-0042 E-mail "awihcourt1@hotmail.com" website "http://awihcourt1.6te.net"
  
 
 
 
 

 
 
ዜና - News

 

ከ26 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስጥ የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ወጣ ---

ከፍተኛ ፍ/ቤቱ በ2ዐዐ3 ዓ/ም ባደረገው ከፍተኛ የሥራ እንቅስቃሴ ከ26 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተወዳድሮ 1ኛ ደረጃ ማግኘት ችሏል፡፡

የአዊ ዞን ሲቨል ሠርቪስ ዋና መምሪያ በዞኑ ውስጥ ያለውን የሴክተር መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ የማወዳደሪያ መስፈርት በመላክ እና ድጋፍ በማድረግ ከቆየ በኋላ የውድድር ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም ውጤት መሠረት የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት 89.5 በማምጣት በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ 26 ሴክተር መስሪያ ቤቶች 1ኛደረጃንማግኘትችሏል፡፡
    

የኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍተት ማተካከያ ስልጠና ተሰጠ

በአዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስር ከሚገኙ ደጋፊ ሂደቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የICT ደጋፊ የሥራ ሂደት ከሰው ኃይል ጋር በመተባበር ከዞን እስከ ወረዳ ፍ/ቤት ከኮምፒውተር ጋር ለሚሠሩ ባለሙያዎች የኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍተት ማስተካከያ ስልጠና ከጥቅምት 18-19/2ዐዐ4 ዓ/ም ለ19 ሴት ለ1 ወንድ በድምሩ ለ2ዐ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በዋናነት በስልጠናው ትኩረት የተደረገበት ብዙ ጊዜ ኮምፒውተር ላይ በሚሰሩ ባለሙያዎች ላይ የሚታዩ 1ዐ /አስር/ የኮምፒውተር አጠቃቀም ክፍተቶችን
በመለየት  ማለት፡-

  1. የፋይልና የፎልደር ስም አሰጣጥ ክፍተት፣
  2. የፎልደር አዘገጃጀት ክፍተት፣
  3. የፋይል ማስቀመጫ ቦታዎች ያለመለየት ክፍተት፣
  4. የፋይል ኮፒ ወይም ባክ አኘ ያለመውሰድ ክፍተት፣
  5. የደረት፣የጠረጴዛ እና የበር ባጆችን የማዘጋጀት ክፍተት፣
  6. የኮምፒዉተር ቫይረስ መተላለፊያዎችን ያለመለየት ክፍተት፣
  7. ኮምፒውተርን በመጠቀም ፋክስ መላክና ያለመቀበል ክፍተት፣
  8. ብሮሸር እንዲሁም የደብዳቤዎች ሂደርና ፉተር አዘገጃጀት ክፍተት፣
  9. በተዘረጉ አካባቢያዊ ኔትዎርክ አማካኝነት መጠቀም የሚቻልባቸውን አገልግሎቶች ያለመጠቀም ክፍተት፣
  10. የኢሜል እና የዌቭሳይት የአድራሻ ዓይነቶችን ያለመጠቀም ክፍተት ናቸው፡፡

በእያንዳንዱ ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲያዝ በማድረግ ከዞን እስከ ወረዳ ፍ/ቤት ትልቅ በባለሙያዎች ላይ የማታይ የአሰራር ክፍተት ማስተካከል የሚያስችል ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡

በቀስት እና በጩቤ ወግቶ 12 ዓመት ህፃን የገደለው ግለሰብ …

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስር በሚገኘው በጃዊ ወረዳ ደቅ ወርቅ ሀገረ ቀበሌ ኩያስ በሚባለው ጐጥ ህፃን ወለላው ደስታ የተባለውን የ12 ዓመት ህፃን ልጅ በቀስት እና በጩቤ የተለያየ የሰውነቱን ክፍል በመውጋት የገደለው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ከቀኑ በግምት 10፡ዐዐ ሰዓት በደቅ ወርቅ ሀገረ ቀበሌ ኩያስ በሚባለው ጐጥ ነሐሴ 16 ቀን 2001ዓ.ም  አበበ ህፅ  የተባለው ተከሣሽ  ህፃን ወለላው ደስታን በቀስት እና በጩቤ የተለያየ የሰውነቱን ክፍል በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገ ሲሆን በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

በዚህም መሠረት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በጓንጓ ወረዳ በሚያስችለው ተዘዋዋሪ ችሎት በፖሊስ ተጣርቶ የዐቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶ በማስረጃ ካጣራ በኋላ ጥቅምት 1 ቀን 2ዐዐ4 ዓ/ም ተከሣሹ በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የወንጀል ችሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሽታነህ እያሱ ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ለሆኑት አቶ መንግስቱ ደነቀው ገልፀዋል፡፡

 7 /ሰባት/ የከፍተኛ ፍ/ቤቱ የሥራ ሂደቶች በፋግታ ወረዳ የ2 ቀን ስልጠና ሰጡ ፡-

በፍርድ ቤቶች ያለውን የአሰራር ክፍተት ለመሙላት ከወረዳ ፍርድ ቤት እስከ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለውን የአሰራር አንድ ለማድረግ የ2 ቀን ስልጠና በፋግታ ለኮማ ወረዳ ፍ/ቤት ከጥቅምት 18-19/2ዐዐ4 ዓ/ም ድረስ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣ በስልጠናው የተሣተፉ  ብዛት ወንድ 58 ሴት 46 ድምሩ 1ዐ4 ሰራተኞች ስልጠናውን ወስደዋል፡፡
እነሱም በስልጠናው የተሳተፉ ሂደቶች ፡-

የሰው ኃይል ደጋፊ የሥራ ሂደት፣ የወንጀል እና የፍታብሔር ዋና የሥራ ሂደት፣የህዝብ ግንኙነት ደጋፊ የሥራ ሂደት፣ የውጥ ኦዲት ደጋፊ የሥራ ሂደት፣ የቅሬታ ሰሚ ደጋፊ የሥራ ሂደት፣ የICT ደጋፊ የሥራ ሂደት ናቸው፡፡

የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የስልጠናውን መጀመር ያበሰሩት የሰው ኃይል ደጋፊ የሥራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አስፋው ይታየው እንደተናገሩት በዚህ አጭር ቀን ውስጥ በቂ የሆነ ስልጠና ይሰጣችኋል ባይባልም ሥራ በምትሰሩበት ጊዜ የሚያጋጥማችሁን ችግር ጭምር በማንሣት እንድትወያዩ በማለት አሳስበው ሁሉም ሂደቶች ወደተዘጋጀላቸው የስልጠና ቦታ ተንቀሳቅሰው አንድ ቀን ተኩል /1/2 በተናጠል ስልጠናውን ከወሰዱበኋላ የግማሽ ቀን የጋራ ውይይት ተደርጐ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የሚቀርቡ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሣት እና በተነሱትም ጥያቄዎች ላይ ምላሽ በተሰጥቶባቸው በኋላ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት በተወካያቸው በኩል የተላከውን የመዝጊያ ንግግር በማድረግ በተሣካ ሁኔታ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

የመንግስትን ገንዘብ ለግልጥቅም ያዋሉ ግለሰቦች  …

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስር በሚገኘው በጓንጓ ወረዳ መንታውሃ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ገንዘብ ያዥ በመሆን ይሰሩ የበሩ 2 ግለሰቦች በከባድ ዕምነት ማጉደል ወንጀል ተከሰው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ተከሳሾች 1ኛ አዲሱ አግደው 2ኛ ወለሊ ደሳለኝ የተባሉት ግለሰቦች በማዘጋጃቤት ይሰሩ በነበረበት ጊዜ ኦዲት ምርመራ ሲደረጉ 1ኛ ተከሳሽ በእጁ የሚገኘውን የመንግስት ገንዘብ 26371.45 ፣ 2ኛ ተከሳሽ በእጁ የሚገኘውን የመንግስት ገንዘብ 3692.50 ለግል ጥቅም በማዋላቸው የአብክመ ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አጣርቶ ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን፡-
በዚህም መሠረት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በጓንጓ ወረዳ በሚያስችለው ተዘዋዋሪ ችሎት በማስረጃ ካጣራ በኋላ ጥቅምት 10 ቀን 2ዐዐ4 ዓ/ም 1ኛው ተከሳሽ  በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 3000 ብር ፣2ኛ ተከሳሽ በ1 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ5ዐዐ ብር  እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን የወንጀል ችሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሽታነህ እያሱ ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ለሆኑት አቶ መንግስቱ ደነቀው ገልፀዋል፡፡

ልጇን የውሃ ጉድጓድ ውስጥ የጨመረች እናት

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስር በሚገኘው በጃዊ ወረዳ ፈንደቃ ከተማ ዐ1 ቀበሌ ህፃን ልጇን የውሃ ጉድጓድ ውስጥ የጨመረች እናት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

ከቀኑ 6፡ዐዐ ሰዓት በፈንደቃ ከተማ ዐ1 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጨረቃ በር በተባለ ቦታ ሰኔ 17 ቀን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ከሚገኘ የውሃ ውድጓድ ውስጥ ተከሣሿ አባየነሽ ዋሴ ህፃን ወንድ ል    ጇን በፎጣ መሰል ጨርቅ በመጠቅለል እና በመጨመር ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገች እና እንዲሁም እራሷን በመደበቅ ከአካባቢ ተሰውራ የነበረ ሲሆን በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር ልትውል ችላለች፡፡

በዚህም መሠረት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በጓንጓ ወረዳ በሚያስችለው ተዘዋዋሪ ችሎት በፖሊስ ተጣርቶ የዐቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶ በማስረጃ ካጣራ በኋላ ጥቅምት 6 ቀን 2ዐዐ4 ዓ/ም ተከሣሿ በ3 ዓመት ፅኑ እስራት እንድተቀጣ የተወሰነባት መሆኑን የወንጀል ችሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሽታነህ እያሱ ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ለሆኑት አቶ መንግስቱ ደነቀው ገልፀዋል፡፡

ከባድ ውብድና የፈፀሙ 3 ተከሳሾች …

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስር በሚገኘው በጃዊ ወረዳ በጃይማላ ቀበሌ ሞሰቢት በሚባለው ጐጥ ውስጥ አቶ ፍቅር የኋላ የተባለውን ግለሰብ በግምት ከቀኑ 5፡00 ስዓት አካባቢ ወደ ቤቱ በሚሄድበት ጊዜ ከባድ ውምብድና የፈፀሙ ተከሳሾች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

1ኛ ተከሳሽ ፍቅር ይልቃል 2ኛ ተከሳሽ አይተነው ነጋ 3ኛ ተከሳሽ መለሰ አድማሱ የተባሉ የካቲት 1ዐ ቀን 2ዐዐ3ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 ስዓት አካባቢ ወደ ቤቱ በሚሄድበት ጊዜ ጨካ ውስጥ ተደብቀው በመቆየት ግለሰቡን በማሰፈራራት በኪሱ የነበረውን 25 ብር እና 3 የገላ ሳሙና በመውሰድ የከባድ ውምብድና ወንጀል ፈፅመዋል፡፡
 

በዚህም መሠረት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በጓንጓ ወረዳ በሚያስችለው ተዘዋዋሪ ችሎት በፖሊስ ተጣርቶ የዐቃቢ ህግ ክስ ተመስርቶ በማስረጃ ካጣራ በኋላ ጥቅምት 3 ቀን 2ዐዐ4 ዓ/ም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ2 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን የወንጀል ችሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሽታነህ እያሱ ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ለሆኑት አቶ መንግስቱ ደነቀው ገልፀዋል፡፡
 
 
 
 
ዝንቅ
   
   
   
 
             

About Awi zone High court | News| Address | Contact Us |

Design By: SHMELES BELACHEW ©2004E.C Awi zone High court

Free Web Hosting